ኢትዮጵያ እንደ ዮጎዝላቪያ ትበተናለች የሚሉ አካላት ተሳስተዋል ይልቁንም የገጠማትን ችግር በድል ትሻገራለች ቲቦር ናዥ
ኢትዮጵያ እንደ ዮጎዝላቪያ ትበተናለች የሚሉ አካላት ተሳስተዋል የገጠሟትን ችግሮች በድል ትሻገራለች ሰላሟንም ትመልሳለች ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የነበሩት ቲቦር ናዥ ገለጹ።
ቲቦር ናዥ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያ እንደ ዮጎዝላቪያ ትበተናለች የሚሉ አካላት መሳሳታቸውን ገልጸዋል።
ዮጎዝላቪያ የአንደኛውን የአለም ጦርነት ባሸነፉ አገራት የተመሠረች ሀገር መሆኗን አስታውሰው ኢትዮጵያ ከ2ሺ አመታት በላይ ፈተናዎችን አልፋ በጽናት የቆየች አገር መሆኗን ተናግረዋል።
አሁንም የገጠሟትን ፈተናዎች በድል በመወጣት ሰላሟን እንደምታረጋግጥ ብሎም ወደ ቀደመ የእድገት ጉዞዋ እንደምትመለስ ነው ያመለከቱት።