የአሸባሪውን ህወሓት የባንዳነት ተግባር በመቀልበስ ሀገራዊ አንድነትና ሰላም ማረጋገጥ እንችላለን
ከህዝብ ጋር በመሆን የአሸባሪውን ህወሓትን የባንዳነት ተግባር በመቀልበስ ሀገራዊ አንድነትንና ሰላምን ማረጋገጥ እንችላለን ሲሉ በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ።
የአፋር ህዝብ በሀገር ሉአላዊነት ላይ የመጣ የውጭ ወራሪን አሳፍሮ የመመለስ አኩሪ ታሪክ ያለው ኢትዮጵያዊ ነው።
ፓርቲዎቹ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትናንት በሠመራ ከተማ በመከሩበት ወቅት እንዳሉት፤ ለክልሉ ህዝብ አንድነትና ሰላም ከመንግስትና መከላከያ ሠራዊቱ ጋር ተቀራርበው እየሠሩ ነው።
የብልጽግና ፓርቲ የአፋር ክልል ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኢሴ አደን ፤ አሸባሪው ህወሓት በበላይነት ሀገር በመራባቸው ዓመታት በአፋር ህዝብ ላይ ተቆጥሮ የማያልቅ ግፍና በደል መፈጸሙን አስታውሰዋል።
የአፋር ነጻ አውጭ ግንባር ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሀሰን ዳውድ በበኩላቸው፤ “ጁንታው በአፋር ክልል ላይ የፈጸመው ወረራና ጭፍጨፋ ቡድኑ በደረሰበት ፖለቲካዊ ኪሳራ ተስፋ መቁሩጡን ያሳያል” ብለዋል
የጀመረው የሀገር ክህደትና አጥፍቶ የመጥፋት ተግባር ህወሓት ሀገርና ህዝብ ወዳድ እንዳልሆነ በተጨባጭ ማሳያ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
“የአፋር ህዝብ የሀገሩን ዳር ድንበር ሳያስደፍር የውጭ ወራሪዎችን መክቶ በመመለስ በኢትዮጵያ ሉአላዊነት ላይ ፈጽሞ እንደማይደራደር ታሪክ ህያው ምስክር ነው”