የአሸባሪው ህወሓት እና በስሩ ያሰለፋቸው ሚሊሻዎች በትግራይ ክልል ባሉ የኤርትራ ስደተኞች ላይ እያደረሱ ያሉትን ጥቃት እንዲያቆሙ የአሜሪካ መንግስት አሳሰበ
የአሸባሪው ህወሓት እና በስሩ ያሰለፋቸው ሚሊሻዎች በትግራይ ክልል ባሉ የኤርትራ ስደተኞች ላይ እያደረሱ ያሉትን ጥቃት እንዲቆሙ የአሜሪካ መንግስት አሳስቧል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች በተለይ በኤርትራ ስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት እየፈፀመ ስለመሆኑ ተጨባጭ ማስረጃዎች እንዳሉት አስታውቋል።
በክልሉ በሚገኙ ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዎች እና በሰብአዊ ድጋፍ በመስጠት ላይ በተሰማሩ ተቋማት ሰራተኞች ላይም የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም የአሜሪካ መንግስት በመግለጫው አሳስቧል።