You are currently viewing ህዝቡ አንድነቱን በማጠናከር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ለክልል የፀጥታ አካላት ያለውን ድጋፍ በተግባር ማረጋገጥ ይገባል- የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

ህዝቡ አንድነቱን በማጠናከር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ለክልል የፀጥታ አካላት ያለውን ድጋፍ በተግባር ማረጋገጥ ይገባል- የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

  • Post comments:0 Comments
ህዝቡ አንድነቱን በማጠናከር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ለክልል የፀጥታ አካላት ያለውን ድጋፍ በተግባር ማረጋገጥ ይገባል- የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ።
የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች አሸባሪው ህወሓትን የሚቃወምና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላ ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አዲስአለም በዛብህን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ ሀገር ሽማግሌዎች እና አባገዳዎች ተገኝተዋል።
በሰልፉ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ባደረጉት ንግግር የህውሀት አሸባሪ ቡድን መንግስት ለትግራይ ህዝብ ሲል በተናጥል ያወጀውን የተኩስ አቁም ስምምነት አጋጣሚነት በመውሰድ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ትንኮሳ እና የሽብር ተግባር እያካሄደ ይገኛል።
አሸባሪው ቡድን ህፃናትን እና እናቶችን ለጦርነት በመማገድ እንደወትሮው ለስልጣን እንጂ ለህዝብና ሃገር ግድ እንደሌለው በተግባር እያሳየ ይገኛል ብለዋል።
“በመሆኑም መላው ህዝባች አንድ ሆኖ ያፀኗት ሀገራችንን በከሀዲዎች እንደማትበታተን እና ለየትኛውም ሀይል እንደ ማትንበረከክ ትምህርት ሊሆን በሚችል መልኩ እስከ መጨረሻ እልባት መስጠት ይገባናል”። ብለዋል
መላው ህዝብም አንድነቱን በማጠናከር በተለይም ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ለክልል የፀጥታ አካላት ያለውን ድጋፍ በተግባር ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የክልሉ መንግስትና ህዝብ ሠራዊቱ ህግን ለመስከበርና በፀረ-ሠላም የሽብር ሃይሎች ላይ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በተካሄደው ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎች እንዳሉት ለሀገር ሉአላዊነት እና ለዜጎች ክብር እራሱን በጀግንነት እየተዋደቀ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፋችንን እናጠናክራለን።
ድጋፍ ከማጠናከር ባሻገር እስከ ግዳጅ በመዝለቅ ከሰራዊቱ ጎን ለመሰለፍና ጁንታውን ለመደምሰስ ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀዋል።
በሰልፉ ላይም ነዋሪዎቹ “እኛ የመከላከያ ደጀን ነን!”፤ “ለመከላከያ ሰራዊታችን ተከፍሎ የማያልቅ ውለታ አለብን!”፤ “የኢትዮጲያን ክብር አሳልፎ የሚሰጥ ትውልድ የለም!”፤ “የጦር መሣሪያ ከትግራይ ሕፃናት ትከሻ ይውረድ!”፤ “የህወሃት ጁንታ ቡድን የኢትዮጵያን ጠላት ነው!” የህዳሴ ግድብ ጉዳይ የሀገራችን የመኖርና አለመኖር ጉዳይ ነው” የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አዲስአለም በዛብህ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች እንዲሁም በክልሉ ከገጠርና ከተማ የተሰባሰቡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ምላሽ ይስጡ