You are currently viewing “የአማራ ክልል የህወሓት የሽብር ቡድን ትንኮሳን ለመመከት ዝግጁ ነው”፦ አቶ አገኘሁ ተሻገር

“የአማራ ክልል የህወሓት የሽብር ቡድን ትንኮሳን ለመመከት ዝግጁ ነው”፦ አቶ አገኘሁ ተሻገር

  • Post comments:0 Comments
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ክልሉ ከህወሓት የሽብር ቡድን የሚፈፀምበትን ትንኮሳ ለመመከት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን የገለፁት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ ነው።
የክልሉን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ የህወሓት የሽብር ብድን የሚፈፅመው ትንኮሳን ለመመከት የአማራ ክልል ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር መንግስት የወሰነው የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ በተራዘመ ግጭት የሚመጣውን ችግርና ጫና ያስቀረ ነውም ብለዋል።
ክልሉ ከ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኋላ ወደ መደበኛ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎቹ መመለሱን ተናግረዋል።
የክረምት እርሻ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ከ4.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ምርት ይጠበቃል ብለዋል። ለኩታ ገጠም እርሻ ልዩ ትኩረት መሰጠቱንም ገልጸዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም 2 ቢሊዮን ገደማ ችግኞችን ለመትከል እየተሰራ ነውም ብለዋል።

ምላሽ ይስጡ