የዘንድሮው አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ
ኢትዮጵያን እናልብሳት በሚል መሪቃል 6 ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኞች የሚተከሉበት የአረጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ተጀመረ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሶስተኛውን አገር አቀፍ የአረጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ይፋ ሲያደርጉ፤ “በኢትዮጵያ በደን የተሸፈኑ አረንጓዴ ተራሮችንና የለመለሙ መስኮችን ማየት ብርቅ ሁኗል፡፡ ኢትዮጵያ ተራቁታለች፡፡ ስለሆነም ኢትዮጵያን ክብሯን፣ ሞገሷንና ውበቷን በጋራ እናልብሳት” ብለዋል፡፡
“በክልል፣ በሀይማኖት፣ በዘርና በጾታ ሳንለያይ በጋራ አገራችን አረጓዴ አሻራችንን በማሳረፍ ለመጪውና ለአሁኑ ትውልድ ምቹ አገር እንፍጠር” ብለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ በአገር አቀፍ ደረጃ 6 ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ መያዙን የተገለጸ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተጀመረ ባለፉት ሁለት ዓመታት ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኞች መተካላቸው ተገልጿል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጸህፈት ቤት በተካሄደው የዛሬው መርሀ ግብር የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።