የብልፅግና ፓርቲ እንደ ፓርቲ ትኩረት ከሚሰጣቸው እሴቶች መካከል የወንድማማችነት እሴት አንዱ ነው፡፡ ይህ እሴት ብዝሀነትን አክብራ በምትኖር እንደ ኢትዮጵያ ባለች ሀገር በእጅጉ ጠቃሚ ከመሆኑም ባሻገር በሁሉም አካባቢዎች የሚከበሩ ሐይማኖት፣ባህልና እሴቶችን እውቅና በመስጠት ማህበራዊ እሴቶችን ማጎልበትና የህዝቦችን ማህበራዊ መስተጋብር ማጥበቅ ይችላል።
የወንድማማችነት እሴት ከሰነድ ውይይት አልፎ በተግባር እንዲተገበር ብልፅግና እንደ ፓርቲ አበክሮ ይሰራል፡፡ ምክንያቱም ወንድማማችነት መቻቻልና አንድነትን፣ፍቅርንና መተሳሰብን፣አለሁ ባይነትን የሚያጎለብት በመሆኑ ነው፡፡ ለዚህ ተፈጻሚነት ደግሞ መላው የፓርቲው አመራሮች፣አባላትና ደጋፊዎች ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ይሰራሉ፡፡
ኢትዮጵያ በርካታ ብሄር ብሔረሰቦች በጋራ የመሰረቷት ሀገር እንደመሆኗ መጠን አንዱ የሌላውን ሐይማኖት፣እሴትና ባህል ማወቁና ማክበሩ ጠንካራ ማህበራዊ ግንኙነትን ከመፍጠርም በላይ የምንሻትን የበለጸገች ኢትዮጵያ ለማየት ያስችለናል፡፡
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ