You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

ብልጽግና ፓርቲ መጪውን አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረገ

በውይይቱ ላይ ከአንድ መቶ በላይ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አመራሮችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ፣በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት  የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ ተገኝተዋል፡፡

መጪው ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅና አገራችን ወደ እውነተኛ የዴሞክራሲ ስርዓት እንድትሸጋገር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበው በተለይም በአገር ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው እንደ ሚድሮክ ያሉ ግል ዘርፍ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ሚና በጣም ትልቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ወ/ሮ አዳነች ሁለንተናዊ የሰው ልጆች ፍላጎት በምሉዕ እይታ ለማሟላት የሚተጋውን ፣የህብረ ብሔራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ተምሳሌት ሆነውን ብልጽግና ፓርቲን በመምረጥ የአገራችንንና ዜጎችን ብልጽግና እናረጋግጥ የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በመጪው ምርጫ ሰላም እንዲያሸንፍ፣ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ፣ህዝብና ሀገር እንዲያሸንፍ የሚድሮክ አመራሮችና ሰራተኞች ቀዳሚ ሚና በመጫወት ለአገራችን ትንሳኤ አሻራቸውን እንዲያኖሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ በበኩላቸው ብልጽግና ፓርቲ የሚከተለው የኢኮኖሚ ፕሮግራም እንደ ሚድሮክ ላሉ የግሉ ዘርፍ ኩባንያዎች እጅግ በጣም ትልቅና መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር መሆኑን አውስተው የግሉ ሴክተር እንዲተናከር፣ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ፣ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የተቋማቱ ሰራተኞችና የአገሪቱ ዜጎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ብልጽግና ፓርቲ በልዩ ትኩረት የሚሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በኢኮኖሚው ውስጥ የሚታዩትን መዋቅራዊ ችግሮች በመፍታት የኑሮ ውድነት ችግርን በመቅረፍ ዜጎች የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ እንደሚሰራ አመልክተዋል፡፡

ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የህዝብና ውጭ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ በበኩላቸው እኛ ኢትዮጵያዊያን የብሔር፣የሐይማኖት፣የቋንቋ የባህልና ሌሎች ብዝሃነት መገለጫዎች ቢኖሩንም ሁላችንም ወንድማማቾች ፣እህትማማቾች በመሆናችን ኢትዮጵያም እናታችን ስለሆነች እና ልጆቿ ተከባብረንና ተጋግዘን መጪው ምርጫ ሰላማዊ፣ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በማድረግ ጠንካራ፣ ለውስጥና ለውጭ ፈተናዎች የማትበገርና ለመጪው ትውልድ የምትመች ሃገር እናድርጋት ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ብልጽግና ፓርቲ እናታችን ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ አበክሮ የሚታገል ፓርቲ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አብነት ገ/መስቀል በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት ሚድሮክ ኢትዮጵያም ሆነ ሌሎች የአገሪቱ የግል ኩባንያዎች አገር ሰላም ሲሆን፣ዜጎች በሰላም ወጥተው ሲገቡ ተጠቃሚ እንደሚሆኑና ለአገርና ለዜጎች ሰላም፣ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ ህይወት መሻሻል በቁርጠኝነት ከሚሰራ ፓርቲ ጎን እንደሚቆሙ በአጽንኦት አብራርተዋል፡፡

በመድረኩ ላይ አስተያየት የሰጡ የኩባንያው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሰላምን፣ ልማትን፣  ወንድማማችነትን፣ህብረ ብሔራዊ አንድነትና ለአገራችን ትንሳኤ ለሚሰራ ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል፡፡

ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ