ፕሮጀክቱ አሥራ ስድስት የሚሆኑ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈና በሀገራችን የዓለም አቀፍ ንግድ ሂደትንና የሎጂስቲክስ ሥርዓትን በማዘመን፣ ኢኮኖሚያዊ ተወዳዳሪነታችንን በማሳደግ በኩል ሊተካ የማይችል ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። ፕሮጅክቱ አስመጪውች እና ላኪወች በየተቋማቱ መሄድ ሳያስፈልጋቸው በሚቀርብላቸው የኤሌክትሮኒክስ አግልግሎት አማካኝነት ለማስመጣት ወይም ለመላክ የሚያስፈልጉ የንግድና ተያያዥ ሂደቶችን በቢሮ፣በቤት ወይም በአመች ቦታ ሆኖ ለመፈጸም ያስችላል፤ በዚህም ይወጣ የነበረውን፣ ወጪ፣ ጊዜና ድካም ማዳን ይቻላል። የገቢና የወጪ ሂደት የሚወስደውን ጊዜ ከ 44 ቀናት በመጀመሪያ ምዕራፍ ወደ 13 ቀናት በሁለትኛ ምዕራፍ ደግሞ ወደ 3 ቀናት ይቀንሳል፡፡ ፕሮጅክቱ የንግድ ሂደቱን የሚተነበይ ያደርገዋል፣የህግ ተገዥነትን ያሳድጋል ፤የሙስና ተግባራትን ለማስቀረት ያስችላል፤ በዚህም ከፍተኛ ወጭ ማዳን ይቻላል።
