You are currently viewing በብልጽግና ወጣቶች ሊግ አዘጋጅነት በሀገር ደረጃ በከተሞች እየተካሄደ ያለው አንደኛው ዙር ምክንያታዊ የወጣቶች የውይይትና ሙግት መድረክ/Youth Reasonable Dialogue ዛሬ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተሞች እየተካሄደ ነው

በብልጽግና ወጣቶች ሊግ አዘጋጅነት በሀገር ደረጃ በከተሞች እየተካሄደ ያለው አንደኛው ዙር ምክንያታዊ የወጣቶች የውይይትና ሙግት መድረክ/Youth Reasonable Dialogue ዛሬ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተሞች እየተካሄደ ነው

  • Post comments:0 Comments

በብልጽግና ወጣቶች ሊግ አዘጋጅነት በሀገር ደረጃ በከተሞች እየተካሄደ ያለው አንደኛው ዙር ምክንያታዊ የወጣቶች የውይይትና ሙግት መድረክ/Youth Reasonable Dialogue ዛሬ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተሞች እየተካሄደ ነው

በመድረኩ ከከተሞቹ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ምሁራን ወጣቶች እየተሳተፋበት ሲሆን የሀገረ መንግስት ግንባታና የወጣቱ ሚና በሚል ርዕስ የተሰናዳ መሆኑ በመድረኮቹ ተገልጿል።


የሀገረ መንግስት ግንባታ ምንነት፣የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደትና ትምህርት የሚወሰድባቸው ጉዳዮች፣የሌሎች ሀገራት የሀገረ መንግስት ግንባታ ልምዶች፣ለውጡና የሀገረ መንግስት ግንባታ እርምጃዎች እንዲሁም የተጠናከረ የሀገረ መንግስት እውን ማድረግ ይቻል ዘንድ የወጣቱ ሚና በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እየተደረገበት ነው።


ብዝሀነታችንን ጠብቀን አንድነታችንን የምናጠናክርባት፣ሰላምና ብልጽግና የተረጋገጠባት፣ዜጎች በእኩልነት ተንቀሳቅሰውና ሰርተው ህይወታቸውን የሚመሩባትን ኢትዮጵያ ማጠናከር ይቻል ዘንድ ሀገረ መንግስቱ ሊቆምባቸው የሚገባው ምሰሶና የወጣቱ ሚናም በሰፊው እየተመከረበት ስለመሆኑ ከየከተሞቹ ብልጽግና ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ነው።


በመድረኮቹ የየከተሞቹ ከፍተኛ አመራሮች ከዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የተወጣጡ ምሁራን ወጣቶች የተነኙ መሆኑ ተገልጿል፡፡


በየከተሞቹ በተዘጋጀው መድረክ የየከተሞቹ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ለተሳታፊ ወጣቶች መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምላሽ ይስጡ