ብልፅግና ፓርቲ ወጥ አሰራር ለመፍጠር የሚያስችሉ መመሪያዎች ማዘጋጀቱን አስታወቀ
ብልፅግና ፓርቲ ወጥ የሆነ አሰራርና ውስጠ ዴሞክራሲ የጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል መመሪያዎች መዘጋጀታቸውን የፓርቲው ማዕከላዊ ቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኙ ኮሚሽነር ኢንጅነር አወቀ ኃይለማርያም እንዳስታወቁት ፤ የብልፅግና ፓርቲ ውህድ ከመሆኑ በፊት የቁጥጥርና የኢንፔክሽኑ ስራ የተዳከመና ምንም አይነት ስራ ሲያከናውን አልነበረም።
የቁጥጥርና የኢንስፔክሽኑ ስራም በአራት ክልሎች ብቻ የተወሰነ እንደነበር ያመለከቱት ኢንጅነር አወቀ ፣ ይህን ሁኔታ ለመቀየር ወጥ አሰራር ሊፈጥር የሚችሉ የተግባር መመሪያዎች መ፣ ዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
መመሪያዎቹ ወደ ተግባር ሲገቡ ብልፅግና ፓርቲ የሚያከናውናቸውን ተግባራት፣ ውስጠ ዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲሁም አንድ ወጥ የሆነ አሰራር ለመፍጠር እንደሚያግዝ ጠቁመው፣ የፓርቲው አመራሮችና አደረጃጀቶች በተቀመጠው ህገ ደንብ መሰረት ስራቸውን ማከናወን አለማከናወናቸውን ለማረጋገጥ እንደሚረዳም አመልክተዋል።