የከተማና የክ/ከተማ የዘርፍ አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮችና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያዩየአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ አለሙ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት በጁንታው የህወሀት ቡድን በአገር ላይ የተቃጣውን ጥፋት ማለፍ ብቻ ሳይሆን የህግ የበላይነትን የማስከበርና ህገ ወጥነትን የመከላከል ተግባራትን ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡
በዚህም የከተማዋን ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ እና የብልፅግና ጉዞዋን በማፍጠን ፈተናዎችን ወደ ድል መቀየር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡የዘርፍ አመራሮች በቀጣይ ወራት የሚያከናውኗቸውን ዋና ዋና ግቦች ያቀረቡ ሲሆን ለተፈፃሚነታቸውም ህዝቡን በማሳተፍ እንደሚረባረቡ አረጋግጠዋል፡፡
ስራዎችን ተቋማዊ በሆነ መልኩ እና በተናበበ መንገድ ለመፈፀም የታየው መልካም ጅምርም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው አቅጣጫ ተወስዷል፡፡ለመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል፡፡