የፅንፈኛው የህወሓት ቡድን እብሪተኝነት የሕዝብ ገንዘብ ከመዝረፍ እስከ ዘር ማጥፋት የደረሰ መሆኑን የአገር መከላከያ ሰራዊት የጦር መኮንኖች ተናገሩ።የቡድኑ የጥፋት እንቅስቃሴ ከዝርፊያ እስከ ዘር ማጥፋት የደረሰ መሆኑን የሠራዊቱ አባላት ይናገራሉ።የህወሓት ጁንታ ቡድን የመጀመሪያውን ጥቃት የፈፀመባቸው የሠራዊቱ አባላት ኮሎኔል አሰፋ አማረ እና ሌተናል ኮሎኔል ደረሰ አየለ የቡድኑን የጥፋት ድርጊት ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።
“ለዚህ ቡድን እጃችንን አንሰጥም” በማለት በጀግንነት በመዋጋት የሚመሩትን ሠራዊት ይዘው በከሃዲው ከታቀደላቸውን የሞት ድግስ በማምለጥ የአገራቸውን ሠላም በማስጠበቅ ላይ ይገኛሉ።ኮሎኔን አሰፋ ሠራዊቱ በቀበሮ ጉድጓድ እየኖረ የትግራይን ሕዝብ በልማት ስራዎች ጭምር እየደገፈ ባለበት በፅንፈኛው ቡድን አሰቃቂ ጥቃት እንደተፈፀመበት የገለፁት በሃዘን ስሜት ነው።
“ህወሓት ተብሎ የሚጠራው ጁንታ ቡድን ካልጠፋ ሕዝብ ሠላም አይሆንም” ሲሉም ነው የገለጹት።ሌተናል ኮሎኔል ደረሰ አየለ በበኩላቸው የቡድኑ አነሳስ ከዝርፊያ እስከ ሕዝብ ጭፍጨፋ የደረሰ ዘግናኝ የአሸባሪነት ተግባር መሆኑን በራሳቸውና ሕይወታቸውን በተነጠቁት ባልደረቦቻቸው ላይ የደረሰውን በደልና ግፍ ጠቅሰው ያስረዳሉ።የጦር መኮንኖቹ የቡድኑ አረመኔያዊ ተግባር የዘረፈውን ገንዘብ በሕዝብ ደም ላይ ተቀምጦ ለመብላት ከማሰብ የመነጨ መሆኑን ተናግረዋል።