You are currently viewing መጥፊያው እየቀረበ የመጣው የማፊያ ቡድን

መጥፊያው እየቀረበ የመጣው የማፊያ ቡድን

  • Post comments:0 Comments

መጥፊያው እየቀረበ የመጣው የማፊያ ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት እየደረሰበት ካለው ሽንፈት የተነሳ በከፍተኛ ሁኔታ የመዳከም እና የመፈረካከስ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል። ይህ ቡድን የመጨረሻ አማራጮቹን ሁሉ ተጠቅሞ እየፈነቀለ ያለው ድንጋይ ሁሉ እንቅፋት እና መጥፊያው እየሆነ ከፍርድም እንደማያስመልጠው እየተረዳው መጥቷል።አሁን የቀረው የመጨረሻ እድል አንድ ነው። እሱም በአስቸኳይ እጅ በመስጠት ህዝብን ከእንግልት እራስንም ከአጉል ውርደት አድኖ በፍርድ አደባባይ መዳኘት ብቻ ነው። መቀሌ የመሸገው ሽፍታ ቡድን እና ያሰማራው ሰራዊት በቀለበት ውስጥ እየተሽከረከረ መውጫው ጨንቆት በሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ሽንፈትን እየተከናነበ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡በነፍስ ግቢ እና ውጪ ውስጥ ሆኖ ዝብርቅርቁ የወጣ መግለጫ መስጠት፣ ሲዘርፍ የኖረውን ጥሪት ሁሉ ለጦር ሜዳ መገበር፣ መከላከያ ሰራዊታችን ላይ የጫረውን እና የፈፀመውን ግፍ ክዶ ቀኑን ሙሉ ተወረርኩ ብሎ ማላዘን መገለጫው ሆኗል።ከምንም በላይ ደግሞ ታሪክ የሚያበላሽ ጦርነት ውስጥ አልሳተፍም ብሎ ለጦርነቱ ጥሪ ጆሮ ዳባ ልበስ ያለው የትግራይ ህዝብ ምላሽ መጨረሻውን እያፈጠነው እና ህዝቡ ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን እየተሰለፈ መሆኑ ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ከቶታል። የትግራይ ህዝብም ባለውለታው ከሆነው የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት ጎን በመሰለፍ የጁንታው ቡድን ግብአተ መሬት እንዲፈፀም የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው።

ምላሽ ይስጡ