በደም ልገሳ ፕሮግራም ላይ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ተገኝተው እንደተናገሩት ለሀገር እና ለህዝብ ክብር ሲል ውድ ህይወቱን እየሰጠ ላለው የጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን የደም ልገሳ በማድረጋችን የሚያኮራ ተግባር ሲሆን ይህም በቀጣይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል:: በደም ልገሳ ላይ የተሳተፉቱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች በበኩላቸው በደም እጦት ሳቢያ የጅግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ክቡር የሆነውን ህይወቱን ለማዳን በሚደረገው ርብርብ ለማገዝ ባደረጉት ድጋፍ መደሰታቸውን ገልፀው በቀጣይም በሌሎች ለመከላከያ ሠራዊታችን በሚደረጉ የድጋፍ ሥራዎች ላይ በከፍተኛ ተነሳሽነት እንደሚሳተፉ ቃል ገብተዋል::
