የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት
የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት
የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ
ወቅታዊ ዜናዎች
መልካም የትንሣኤ በዓል ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች!
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ብልፅግና ፓርቲ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና የአብሮነት እንዲሆን ይመኛል። #prosperity
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል እንኳን አደረሳችሁ። የትንሣኤ በዓል አራት ነገሮች የተሻሩበት ዕለት ነው። ሞት፣ መግነዝ፣ መቃብር እና ማኅተም፣ ሞት እና መቃብር ከአዳም የመጡ ዕዳዎች ናቸው። ወደ አፈር ትመለሳለህ በመባሉ። መግነዝ የወዳጅ፣ ማኅተም የጠላት ናቸው። ሰው በአራቱም [...]
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በትንሣኤ በዓል ዋዜማ 215 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችን ከሙሉ የቤት ቁሳቁስና ከበዓል መዋያ ጋር ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በስጦታ አበረከቱ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን! በማለት ባስተላለፉት መልእክት ሁልጊዜም በበዓላት ወቅት እንደምናደርገው፣ ዛሬ በትንሣኤ በዓል ዋዜማ በከተማችን የተለያዩ አካባቢዎች በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የገነባናቸውን 215 [...]
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ አደም ፋራህ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ አደም ፋራህ ኢብራሂም ለክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። በዓሉ የሰላም፤ የጤና፤ የብልፅግና እንዲሆን ከልብ በመመኘት: መልካም የፋሲካ በዓል እንዲሆን ተመኝተዋል!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትንሳኤ በዓል የመልካም ምኞት መልዕክት ሙሉ ቃል ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል:- እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል [...]
ብሔራዊ ጥቅምን ያስቀደመ ዲፕሎማሲ፡ የኢትዮጵያ ስልታዊ ገለልተኝነትና ዓለም አቀፍ ቁመና
ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በዓለም አቀፍ መድረክ የያዘችው ዲፕሎማሲያዊ አቋም ሉዓላዊነትን የማስከበር ጽናትና ብሔራዊ ጥቅምን ባስቀደመ ስልታዊ ግንኙነት ላይ የተገነባ መሆኑን በተግባር አስመስክራለች። አገራችን በዓለም ፖለቲካ ውስጥ የሚታዩ የጎራ ግጭቶችንና ልዩ ልዩ ጫናዎችን በብልሃት በማለፍ፣ [...]
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለቡሩንዲ ፕሬዝደንት ክቡር ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬን አሸኛኘት አደረጉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቡሩንዲ ፕሬዝደንት ክቡር ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬን ከሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝታቸው በኋላ በቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ሸኝተዋቸዋል። #prosperity
የቡሩንዲው ፕሬዝደንት ክቡር ኤቫሪስቴ ንድያይሽሚዬ የብሔራዊ ቤተመንግስት ሙዚየምን ጎበኙ
የቡሩንዲው ፕሬዝደንት ክቡር ኤቫሪስቴ ንድያይሽሚዬ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው አካል በሆነው በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ሙዚየም ጉብኝት አድርገዋል። በታላቁ ቤተ-መንግስት ጣሪያ ስር የተገናኙት ሁለቱ ወንድማማች ሀገራት፤ በአፍሪካውያን የተጻፈውን ታላቅ ታሪካዊ ቅርስ በጋራ ዘክረዋል! [...]
በመጋቢት 24 የተገኙ የለውጥ ትሩፋቶች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ አስችሏል- አቶ መሐመድ ሁሴን የብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ
በመጋቢት 24 የተገኙ የለውጥ ትሩፋቶች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ አስችሏል ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ ገለፁ። በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ በሀገራዊ ለውጡ ለተመዘገቡ የልማት ድሎች ዕውቅና የሚሰጥ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል። [...]
መጣጥፎች
የአረንጓዴ አሻራ ተግባር ለትዉልድ ተስፋን የመትከል ትልቅ ፕሮጀክት ነዉ
የብልፅግና እሳቤ ስር የሰደደው የሰውን ህይወት በመለወጥ፣ የሀገርን ገጽታ በመቀየር እና ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ላይ ነው። ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ በተግባር ከሚያሳዩን ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል ደግሞ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ግንባር ቀደሙን ስፍራ ይይዛል። የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ተራ [...]
የብልፅግና አዲሱ መንገድ፡ የመደመር ርዕዮት
ኢትዮጵያ፥ የፖለቲካ ጉዟችን ረጅም ታሪክ ውስጥ የሌሎችን ሀገራት ርዕዮተ ዓለም በመቅዳትና ያንኑ ገቢራዊ ለማድረግ ብዙ ጊዜዋን አሳልፋለች። ከሌሎች ሀገራት የተቀዳውን ርዕዮት ለማስከበር ስንል ያገኘነው ውጤት ድህነት፣ ቂምና ቁርሾ፣ መፈራረስ፣ መካረር፣ ጽንፈኝነት እና ውድ የሕይወት መስዋዕትነት መክፈል [...]
"በወንድማማችነት እሴት ላይ የቆመ ህብረ ብሔራዊ አንድነት መገንባት "
በኢትዮጵያ የወንድማማችነት እሴትን ለማጎልበት ፓርቲያችን የመደመር መንገድን ይከተላል፡፡ ፓርቲያችን ብልፅግና የመደመር እሳቤዎችን አንድ በአንድ እየተገበሩ በመሄድም የወንድማማችነት መንፈስን ከተኛበት የሚቀሰቅስ ፓርቲ ነው። "የብሔሮችን ጥያቄ ያከበደው የወንድማማችነት መቅለል ነው"ብሎ የሚያምነው ፓርቲያችን [...]